“ክርስቶስ ሕያው ነው፣ እናንተንም ሕያው እንድትሆኑ ይፈልጋል” 

አዲሱ የር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ  ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን ሕያው ክርስቶስ የሚል መጠሪያን ይዞ በመጋቢት 24 ቀን 2011 . . ታትሞ ይፋ ተደረገ።

የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ከዓለም ዙሪያ ከተወጣጡ ወጣቶች ጋር ሆነው ከመስከረም 23 ቀን እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2011 . . ድረስ በቫቲካን ከተማ በተደረገው የብጹዓን ጳጳሳት 15 ጠቅላላ መደበኛ ጉባኤ ወጣቶች፣ እምነት እና ጥሪያቸውን በጥበብ እና በማስተዋል ተገንዝበው ትክክለኛ እና ቆራጥ ውሳኔን እንዲያደርጉ በሚል ርዕሥ ሰፊ ውይይትን ካደረጉ በኋላ የጉባኤያቸውን ጠቅላላ ሃሳብ ለር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ ማቅረባቸው ይታወሳል። ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስም የጉባኤውን ጠቅላላ ሃሳብ ተቀብለው  በፊርማቸው አጽድቀውታል፡፡

ክርስቶስ ሕያው ነው፣ እናንተንም ሕያው እንድትሆኑ ይፈልጋል በማለት የሚጀምረው የር. ሊ. ጳ.  ቃለ ምዕዳን በርካታ መልዕክቶችን የያዘ መሆኑ ታውቋል። የር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ በቃለ ምዕዳናቸው ቤተክርስቲያንም የወጣቶችን ጥንካሬ፣ አቅም እና እምነትን እንደምትፈልግ መናገራችውን ጠቅሶ ወጣቶች የደረሱበትን ቦታ ደርሰው ወደ ኋላ የቀሩት ካሉ በትዕግስት እንዲጠብቋቸው ማሳሰባቸውን  ገልጸዋል። ቅዱስነታቸው በዘጠኝ ምዕራፎች ከፍለው አስቀምጠዋቸዋል።

ምዕራፍ አንድ፦ የእግዚአብሔር ቃል እና ወጣቶች፣

ምዕራፍ ሁለት፦ ኢየሱስ ሁል ጊዜ ወጣት ነው፣

ምዕራፍ ሦስት፦ እግዚአብሔር ወጣቶችን ለዛሬም ጭምር እንዲሆኑ ጠርቶአቸዋል፣

ምዕራፍ አራት፦ ሦስት ዋና ዋና እውነቶች፣

ምዕራፍ አምስት፦ ምርጫ የሚደረገበት ዕድሜ፣

ምዕራፍ ስድስት፦ የወጣቶች እና የአዛውንት ግንኙነት፣

ምዕራፍ ሰባት፦ የወጣቶች አገልግሎት፣

ምዕራፍ ስምንት፦ ጥሪ

ምዕራፍ ዘጠኝ፦ በጥበብ ማስተዋል፣

ይህ ቃለ ምዕዳን ሙሉውን በPDF በእንግሊዘኛ ቋንቋ አያይዘን አቅርበናል፡፡

synod

የእያንዳንዱን ምዕራፍ ትንተና በተከታታይ ይዘን እንደምናቀርብ እናስታውቃለን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *