ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሊቀጳጳሳት ዘኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ የጣለባቸውን ኃላፊነት በተመለከተ መላው ካቶሊካውያን እና በጎ ፈቃድ ያላቸው በሙሉ ጸሎት እንዲያደርጉላቸው ጥሪ አስተላለፉ

 

ምንጭ፡ አዲስ አበባ ካቶሊካዊ ሰበካ ጠቅላይ ጽ/ቤት
ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ባሳለፍነው ማክሰኞ የካቲት 12 ቀን 2011ዓ.ም. በአዲስ አበባ ካቶሊካዊ ሰበካ ጠቅላይ ጽ/ቤት በመገኘት ከሠራተኞች እና ከጠቅላይ ጽ/ቤቱ ኃላፊዎች ጋር ባደረጉት ውይይት የኢፌዲሪ ሰላም እና ዕርቅ ኮሚሽንን አስመልክቶ መንግስት የጣለባቸውን ኃላፊነት በብቃት እና በኃላፊነት መወጣት እንዲችሉ እና በአገራችን ዘላቂነት ያለው ሰላም እንዲሰፍን መላው ካቶሊካውያን እና በጎ ፈቃድ ያላቸው በሙሉ በዚህ ሥራ እንዲሳተፉ እንዲሁም በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵውያን ያላሰለሰ ጸሎት እንዲያደርጉ አደራ ጭምር ጠይቀዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የካቶሊክ ቲቪ ኢትዮጵያ የአንድ ዓመት አገልግሎት ምን እንደሚመስል፣ ውይይት እና የተመልካቾች አስተያየት መቀበያ ሥነሥርዓት የተከናወነ ሲሆን በቀጣይ የቴሌቪዥን አገልግሎቱ በመዋቅር፣ በሰው ኃይል እና በተጨማሪ ቁሳቁስም የበለጠ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ገንቢ አስተያየቶች ተሰንዝረዋል፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *