የኤርትራ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ከፍተኛ ልዑካን አዲስ አበባ ተገኙ

በብፁዕ አቡነ መንግሥተ አብ ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካውያን ዘኤርትራ የተመራ ልዑካን የካቲት 5 ቀን 2011 ዓ. ም. በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ጽ/ቤት በመገኘት ከብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካውያን ዘኢትዮጵያ ጋር ተገናኙ፡፡በሥነ ሥርዓቱ ብፁዕ አቡነ ሙሴ የእምንድብር ሀገረ ስብከት ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ አንጀሎ የሐረር ሀገረ ስበከት ጳጳስ ተገኝተዋል፡፡ ብፁዕነታቸውን እንኳን ደህና መጡ በማለት የክብር አቀባበል ያደጉላቸው ሲሆን ከብፁዕነታቸው ጋር የመጡትን ከፍተኛ የቤተክርስቲያን ልዑካን ተዋውቀዋል፡፡ በዚህም ጊዜ ክቡር አባ ሐጐስ ሐይሽ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ጠቅላይ ጸሐፊ ስለ ኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን አጠቃላይ ሁኔታ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን የልዑካኑ ቡድን ከ21 ዓመታት በውሃላ ለመጀሪያ ጊዜ ጽ/ቤታችን በመገኘታችሁ የተሰማኝ ደስታ አገልጻለሁ በማለት ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡

በመቀጠልም ብፁዕ ካርዲናል ብፁዕነታቸውንና ልዑካኑን በማመስገን በኤርትራ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ታላቅ ናት ብለዋል፡፡ የሁለቱ ሀገር የጳጳሳት ጉባኤ ለሁለቱ አገራት መልካም ግንኙነት ከፍተኛ ጥረት ያደረጉ መሆኑን ገልጸው “በእግዚአብሔር ፈቃድ ለዚህ ዕለት መብቃታችን ቀላል አይደለም ብፁዕነትዎ እኛን ለመጐብኘት በመምጣታት የተሰማን ደስታ ታላቅ ነው” በማለት ደስታቸውን በኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ስም ገልጸዋል፡፡

ብፁዕ አቡነ መንግሥተአብም ከሁሉ በላይ እግዚአብሔርን አመስግነው የልዑካኑ ቡድን በኢትዮጽያ ከምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጋር ያለውን የተሳሰረ አንድነት የበለጠ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል፡፡ በኤርትራ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በሐዋርያዊ ሥራ ሆነ በማህበራዊ ልማት አገለግሎት በምትችለው ሁሉ ከሕብረተሰቡ ጐን በመቆም ታላቅ ሥራ  እየሰራች መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከሁሉ በላይ ይህ በሁለቱ አገራት የተጀመረው የሰላም ግንኙት ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሁንም ጸሎታችንን አናቋርጥ በማለት በድጋሚ ስለተደገላቸው አቀባበል ምሥጋና አቅርበዋል፡፡ ብፁዕ አቡነ መንግሥተአብ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የሐዋሪያዊ አገልግሎት በመስጠትና በአዲስ አበባ ከተማ በካፑቺን ፍራንሲስካዊያን የፍልስፍና እና ነገረመለኮት ተቋም በማስተማር ቤተክርስቲያንን አገልግለዋል፡፡

 

Eritrean Catholic Church delegates visit Ethiopian Catholic Church

A delegation of the Eritrean Catholic Church led H.G. Archbishop Mengisteab, Archbishop of Asmara and President of the Eritrean Catholic Bishops’ Conference paid a courtesy visit to the Ethiopian Catholic Church on February 12, 2019. The visit took place for the first time in 21 years.

The delegates were met by H.Em. Cardinal Berhaneyesus, CM, Metropolitan Archbishop of Addis Ababa and President of CBCE, H.E. Bishop Mussie, Eparch of Emdibir Gebreghiorgis, H.E. Bishop Angelo Pagano, Apostolic Vicar of Harar, Rev. Fr. Hagos Hayish, CM, ECS Secretary General and others. During the visit the Cardinal and the Archbishop recalled that the Catholic Church had remained as a bridge for the people of both countries even during the time of war. They thanked God for answering the prayers of his people for peace. They called of all Catholic faithful to continue praying for their countries and ask God to make them instruments of peace.

 

 

H.G. Archbishop Mengisteab as a priest had for years served as a Pastoral agent in different parts of Ethiopia including teaching theology at the Capuchin Institute of Philosophy and Theology in Addis Ababa.

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *