ብጹዕ ካርዲናል ብርሃነ እየሱስ ሱራፌል የብሄራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን ሰብሳቢ ሆነው ተመረጡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነ እየሱስ ሱራፌልን የብሄራዊ እርቅና ሰላም ኮሚሽን ሰብሳቢ አድርገው ሾሙ።

ጠቅላይ ሚኒሰትሩ የህግ ባለሙያዋን የትነበርሽ ንጉሴን ደግሞ የኮሚሽኑ ምክትል ሰብሳቢ አድርገው ዛሬ ሾመዋል።

የብሄራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን በሃገሪቱ የተጀመረውን ሁለንተናዊ ለውጥ በማስቀጠል ለውጡ ተቋማዊ ለማድረግ እና ሃገራዊ አንድነትን ለመገንባት በርካታ ስራዎች እንደሚጠበቅበት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተናግረዋል፡፡

የኮሚሽኑ አባላት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር የመጀመሪያ ውይይታቸውን እያካሄዱ ነው፡፡

          

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *