የአቋም መግለጫ

የ19ኛው የምስራቅ አፍሪካ ጳጳሳት ጉባኤዎች ህብረት (አመሰያ) ጉባኤ የአቋም መግለጫ

ክፍል ሁለት…

9. ዲጂታል መገናኛ
በቅድስት መንበር የተቋቋው የመገናኛ ብዙኃን ጽ/ቤት እናደንቃለን። እኛም በቀጠናችን ለሚደረጉ የስብከተ ወንጌል አገልግሎቶች ይህ ጽ/ቤት ለሚያደርገው ተግባር ድጋፋችን እንሠጣለን። በዘመናዊ ዲጂታል መገናኛ ተጠቅመን ስብከተ ወንጌል ማከናወን መጀመሩ በጣም እንደግፋለን።
በየቁምስናዎችና ሀገረ ስብከቶች የዘመናዊ ዲጂታል መገናኛ ብዙኀን ዌብሳይቶች መጠቀም እናበረታታለን። ጋዜጠኞች ለሙያቸው ክብር ፤ታማኞች ኃላፊነት የሚሰማቸው ትክክለኛ ዜና እንዲያወጡ ማበረታታት።
10. ስለ ወጣቶች
ወጣቶች ባላቸው ተነሳሽነት ኃይልና ኃላፊነት ብዝኃነታቸው የዓለም ዜጎች ሆነው ተሻጋሪ ባህል እንዳላቸውና የቤተክርስቲያን አለኝታ መሆናቸውን እናደንቃለን ዕውቅናም እንሠጠዋለን።
ለወጣቶች የሚሆን ቀጣይነት ያለውና ውጤታማ የሆነ ሐዋርያዊ አገልግሎት ለመስጠት ኃላፊነትን እንወስዳልን። በእምነት ጥሪን በመለየትና በሥነ ምግባር ላይ ያተኮረ የእምነት ሥልጠና እንዲያገኙ እንጥራለን።የወጣቶችን ሥራ አጥነትና ችግሮችን ሊያቃልሉ የሚችሉ ፕሮግራሞችን በመንደፍ እንዲሁም ሰላማዊ አንድነታቸው እንዲጠበቅ የአመራር ክህሎታቸውና መንፈሳዊ ሕይወታቸው እንዲያድግ አብሯቸው የሚጓዝ መሪ ካህን በመመደብ እንሠራለን።
11. የተቀናጀ ሥነ ምህዳር (Ecology)
የቅዱስ አባታችን ፍራንሲስኮ ውዳሴ ላንተ ይሁን የሚል መልእክት መንፈስ በተከተለ መልኩ የአመሰያ ቤተሰብ ፍጥረት እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የሰጠው ስጦታ ስለመሆኑ ዕውቅና እንዲሰጥና ለፍጥረት ክብር እንዲሰጥ ጥሪ እናቀርባን።
ሁሉም የሰው ልጆች በአየር መዛባት እንዲሁም የተፈጥሮ ሀብትን በመበዝበዝ፣ ቆሻሻና ብክለት፣ በድህነት ምከንያት እኩል እየተሰቃዩ እንደሆነ እንመሠክራለን። ሁሉም ነገር የተሣሰረ ስለሆነ ማህበራዊ እና የተፈጥሮ ዓለም ለየብቻ ለያይተን ማየት አንችልም።
የተፈጥሮ ሀብትን መጠቀምን ወደጎን መተው እንደማንችል እናውቃለን። ነገር ግን እውነተኛ መሆን አለብን። ማንም የግል ጥቅምን በማስቀደም በስግብግብነት ነገሮችን እውነታዎችን መደበቅ የለበትም። እውነተኛ ግልዕ ገንቢና ታማኝነት ያለው ውይይት መደረግ አለበት። ይህ ውይይት ደግሞ ትብብርን፣ ተደጋጋፊነትን፣ ለጋራ ጥቅም አብሮ መሥራትን የሀብት ዓለም አቀፋዊነትን ለድሆችና ለምድራችን ቅድሚያ የሚሠጥ መሆን አለበት። ሁሉም እናታችን ምድር የጋራ ቤታችን መሆኗን ማወቅ አለበት፡12. ለሁለንተናዊ ሰብአዊ ዕድት ከሚሠሩ ተቋማት ጋር በትብብር ስለመሥራት።
እኛን የሚመስሉ በምሥራቅ አፍሪካ ለምትገኘው ቤተክርስቲያን ራዕይ ለማሳካት አብረውን የሚሠሩ አጋሮቻችንን እናደንቃለን። እንደ አመሰያ ጳጳሳት አመሰያን በአፍሪካና በማዳጋስካር የጳጳሳት ጉባኤዎች ሲምፖዚየም (ሴካም)፣ በተባበበሩት መንግሥታትና ድረጅቶቹ በአፍሪካ ሕብረት፡ በምሥራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ እንዲሁም በኢጋድ የሁለንተናዊ ሰብአዊ ዕድገት በሚመለከት ቁልፍ ሚና መጫወት እንችል ዘንድ በትጋት እንሰራለን።
ይህ ደግሞ መልካም አስተደደር ለማስፈንና ሁለንተናዊ ሰብአዊ ዕድገት በምሥራቅ አፍሪካ ለማምጣት ይጠቅመናል።
በየሀገሩ በሚገኙ የጳጳሳት ጉባኤ ጽ/ቤቶች የፓርላማ ጉዳዮችን የሚከታተሉ ጽ/ቤቶች እንዲኖሩ እና የፓርላማ አባላት ለሆኑ ካቶሊካውያን የአቅም ግንባት እንዲሠራና ይህም ተደርጎ ለሁለንተናዊ ሰብአዊ ዕድገት እንዲሁም ለድሆች ቅድሚያ የሚሠጡ ሕጎች በአመሰያ ሀገራት እንዲወጡ ለማድረግ ያስችላል።
13. ለካህናትና ለገዳማውያን የማህበራዊ ዋስትና ተቋማት ጉዳይ
እንደ አመሰያ ጳጳሳት ካህናትና ገዳማውያን በስብከተ ወንጌልና ተቋማቶቻችን በማስተዳደር የሚጫወቱት ልዩ ሚና እናደንቃለን። ሆኖም ካቶሊክ ተቋማት ሁሉ በሥራቸው የሚሠሩ አገልጋዮችን ማህበራዊ ዋስትና ለማረጋገጥ ከመሠል አጋር ተቋማት ጋር በጋራ መሥራት ይኖርባቸዋል። እንዲሁም ተቋማቶቹ ራሳቸውን የሚችሉባቸውን መንገዶች በማፈላለግ የአገልጋዮችን ማህበራዊ ዋስትና ጉዳይ በተገቢው ሁኔታ እንዲመቻች መሥራት ይኖርባቸዋል።
14. ስደተኞችና ተፈናቃዮች የሚፈልሱ ሰዎች ጉዳይ
ምሥራቅ አፍሪካ የስደተኞች የተፈናቃዮች መጠለያ መሆኗን በሚገባ እናውቃለን። ይህ ደግሞ እየሆነ ያለው ብዝኃነትን በተገቢው መንገድ ማስተናገድ ካለመቻል፣ ሰብአዊ መብቶችን ካለማክበርና ሁሉን ያማከለ የኢኮኖሚ ዕድገት ካለመኖሩ የተነሳ ነው።
ከርዕሰ ሊቀነ ጳጳሳት ፍሪንሲስኮስ ባለን ህብረት መሠረት እርሳቸው ስለስደተኞች ያወጡት ሐዋርያዊ አገልግሎት ዕቅድ እንደግፋለን። የቅድስት መንበር አንዱ ጽ/ቤት የሆነው የሁለንተናዊ ሰብአዊ ዕድገት ጽ/ቤት ለስደኞች የሚያደርገውን ዓለም አቀፍ አቋምና አቅጣጫ ድጋፍ ለመስጠት ራሳችንን አዘጋጅተናል። በምሥራቅ አፍሪካ የሚገኙ ሕዝቦች ሁሉ በወንድማዊ ፍቅር ተነሳስተው ለዚህ አቅጣጫ መሳካት የበኩላቸውን አስትዋፅዖ እንዲያደርጉ ጥረት እናደርጋለን።
15. የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲዎች/ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት
በቀጠናው የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ ተቋማትን እንኮራባችኋለ፤ ዕድገታችሁን እናበረታታለን። የቤተክርስቲያን ተልዕኮ የሆነው የሰው ልጅ ሁለንተናዊ ዕድገት ተግባራዊ ለማድረግ የእናንተ ሚና ቀላል አይደለም። ለዚሁም በካቶሊክ ቤተክርስቲን ማህበራዊ አስተምሮ ላይ ተመስርታችሁ የምታደርጉት ተግባራዊ እንቅስቃሴ የቤተክርስቲያን ተልዕኮ ለመመስከር አጋዝ በመሆኑ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ድጋፋችን ነው። ከሌሎች ወገኖች ጋር በሚደረገው ለጋራ ጥቅምና ዕድገት በጥናት ላይ በተመሰረተ መረጃ ላይ በመመስረት ውይይትንና ተግባቦትን በመፍጠር የአካባቢያችንን ዕድገት ለማሳደግ በሚደረገው እንቅስቃሴ ድርሻችንን ማበርከታችንን እንቀጥላለን።
16. የቤተክርስቲያን ተቋማትን ተጠያቂነት ባለው መንገድ ማስተዳዳር
በአመሰያ ቀጠና የቤተክርስቲያን ተቋማት ንብረቶችን በባለቤትነት መንፈስ የማስተደደር ኃላፊነታችን ታማኝነት ተጠያቂነት ግለፀኝነት በሚያሳይ መልኩ መሆን አለበት።
የአመሰያ ተቋማትን በትክክለኛው መንገድ ይተዳደሩ ዘንድ ፖሊሲ ለማውጣት ትልቅ ምኞት አለን። ከምዕመኖቻችን ተባብረን ያላቸውን አቅምና ልምድ ተጠቅመን በጋራ መሥራት ይኖርብናል። ለዚህም ይረዳን ዘንድ በአመሰያ ቀጠና ደረጃ የካቶሊክ ባለሞያዎች የጋራ መድረክ ለማቋቋም መሥራት እንፈልጋን።ይህም መድረክ መፈጠሩ ስለታማኝነት ስለኦዲት እንዲሁም በቤተክርስቲያን ተቋማት አሰተዳደርና መሪነት ሚና ላይ የምዕመናን ተሳትፎ ለማበልጸግና ልምድ ለመለዋለጥ ይረዳናል።
17. የኃይማኖት አክራሪነት ጽንፈኝነትና ሽብርተኝነት።
ወጣቶችን ከጽንፈኝነትና ከሽብር ጋር በተያያዘ ሁኔታ ብዙ ፈተናዎች እንደሚያጋጥማቸው እንረዳልን። ይህም ሁኔታ በቀጠናችን ሠላምና ደህንነት ላይ ተፅዕኖ ያሳርፋል። ስለዚህ በሐዋርያዊ አገልገሎት ለተሰማሩ አገልጋዮች አቅማቸውን አሳድገን በዚህ ሁኔታ ለሚገኙ ወጣቶች ልዩ ትኩረት ለመሥጠትና ለመንከባከብ እንሠራለን። ሰብአዊ ክብር ሰብአዊ መብት በጠበቀ ሁኔታ ሽብርተኝነትን ከሚታገሉ የመንግሥት ተቋማት ጐን ሆነን እንሠራለን።
18. ሌብነት/ሙስና
በአመሰያ ሀገራት የሚገኙ ሕዝቦች ሁሉ እየተባባሰ ባለው የሙስና ሁኔታ እየተቸገሩ ይገኛሉ። ሙስና የሰው ልጅ ሁለንተናዊ ዕድገትና ሰላማዊ አንድነት የሚጻረር ሁኔታ ነው። ሙሰናን ለመዋጋት ታማኝነትን እና ተጠያቂነትን ማሳደግ ያስፈልጋል።ለዚህም አገልጋዮች የሚያዘጋጁት የምዕመናን ሕንፀት በቤተክርስቲያን ማህበራዊ አስተምህሮ በጥልቀት የሚሠጥ መሆን አለበት። ክርስቲያኖች ሁሉ የታነፀ ንፁህ ህሊና ኖሮአቸው በማህበረሰብ ውስጥ የታማኝነት ምሳሌ ሊሆኑ በሚያስችላቸው መንገድ ሊዘጋጁ ይገባል።
19. የቤተክርስቲይን ሲኖዶሳዊ (አብሮ የመጓዝ) ባህርይ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ፍራንሲስኮስ ስለ ቤተክርስቲያን ሲኖዶሳዊ ባህርይ የሚያስተምሩት ትምህርት በጥልቀት እንረዳለን። ለእርሳቸው ሲኖዶሳዊነት የቤተክርስቲያን መሪነታቸው ማዕከላዊ ሀሳብ ነው። እንደእርሳቸው አስተምህሮ ሲኖዶሳዊነት መሠረታዊ የሆነ የቤተክርስቲያን ባህርይ ነው።
እኛ እንደ እረኞች በአመሰያ ሀገራት አዳማጭ ቤተክርስቲያን መሆን እንፈልጋለን። ምከንያቱም የቤተክርስቲያን የነቢይነት ተልዕኮ ይሳካ ዘንድ የእያንዳንዱ ምዕመን ሀሳብና ተሳትፎ አስፈላጊ መሆኑን ስለምናምን ነው። ይህን ስንል በዚህ አጋጣሚ ለምዕመናኖቻችን ማሳሰብ የምንፈልገው ሲኖዶሳዊነት ማለት የቤተክርስቲያንን ማዕከላዊነትን ማፍረስ ማለት አይደለም።
ሲኖዳሳዊነት ማለት ሁል ጊዜ ከጴጥሮስ ጋር እና በጴጥሮስ ሥር በሙሉ ህብረት ሆኖ በጋራ መጓዝ ማለት ነው።
20. ስለ ልጆች ጥበቃ
ሁሉም ሰው እንዲሁም ልጆች ክብር አላቸው። ለጥቃት ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችና የሕፃናት መደፈርን አጥብቀን እናወግዛለን።ለጥቃት ተጋላጭ ሰዎችና የልጆች ጥበቃ በተመለከተ ያለው የቤተክርስቲያን አሰራርና ደንብ በተከተለ መልኩ ሁሉም የቤተክርስቲያን ተቋማትና ኃላፊነት ያላቸው ሰዎች በሁሉም ፕሮግራሞቻቸው የልጆች ጥበቃና መመሪያ ደንብ ማካተት አለባቸው የልጆች ጥበቃ ጳጳሳዊ ኮሚሽን እና የአመሰያ የሐዋርያዊ ሥራዎች ማስተባበርያ ጽ/ቤት የጳጳሳት ጉባኤዎች ፖሊሲ የሌላቸው ከሆነ ፖሊሲ እንዲያዘጋጅ የሚረዷቸው ተቋማት ናቸው።
21. አዲስ ስብከተ ወንጌል
እንደ አመሰያ ጳጳሳት በምዕመኖቻችን ላይ የክርስትና እምነትና የወንጌል እሴቶች በሕይወታችን ውስጥ እየተንጸባረቀ አለመሆናቸውና ሕያው ብዝነትን ሰብአዊ ክብርን ሰላማዊ አንድት እና ሁለንተናዊ የሰው ልጅ ዕድገት ከግምት ውስጥ ያላስገቡና የሚቃረኑ ነገሮች ሲደረጉ ስንመለከት እናዝናለን። የወንጌል እሴቶችን ከእያንዳንዱ የሰው ልጅ ሕይወት ጋር ማዛመድ ይቻል ዘንድ አዲስ ስብከተ ወንጌል እንደሚያስፈልግ እየተረዳን ነው። አዲሱ ስብከተ ወንጌል ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት ያለው፣ ባህልን የሚያንጽና የሚሰብክ እንዲሆን ነው። ለዚህም አዲስ አካሄድ እና ዲጂታል የስብከተ ወንጌል መንግድ በመጠቀም ነው።
ማጠቃለያ
“በእግዚአብሔር ላይ የተመሠረተ ህያው ብዝኀነትን፣ሰብአዊ ክብርን፣ሰላማዊ አንድነትን”
እንድንለማመድና የጋራ ጉዞ እንዲኖረን በዚህ ጉባኤ የሰበሰበን እግዚአብሔር አምላካችንን እናመሠግናለን። እረኞች እንደመሆናችን መጠን ጸሎታችን እንደማይለያችሁ ቅዱስ ጳውሎስ በፊሊጵስዮስ ለሚገኙ ክርስቲያኖች በጻፈው መልእክቱ “ለሁላችሁም በምጸልይበት ጊዜ ሁሉ ጸሎቴ በደስታ የተሞላ ነው … እናንተ ሁልግዜ በልቤ ናችሁና”(ፊሊ.1፡4፡-7) እንዳረጋገጠው እኛም በድጋሚ እናረጋግጥላችኋለን።
በቅድስት ድንግል ማርያም የእናትነት ጥበቃና አማላጅነት ሥር እንድትሆኑ ለእርሷ ለእግዚአብሔር እናት ለአፍሪካ ንግሥት አደራ እንሰጣታለን።
 
ብፁዕ አቡነ ቻርለስ ካሶንዴ
አዲሱ አመሰያ ሊቀመንበር
ልደተማርያም ካቴድራል
ሐምሌ 15 ቀን 2010 ዓ. ም.
አዲስ አበባ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *