የአቋም መግለጫ : ክፍል አንድ

19ኛው የምሥራቅ አፍሪካ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤዎች ሕብረት ጠቅላላ ጉባኤ
ሐምሌ 6-16 ቀን 2010 ዓ. ም.
በአዲስ አበባ

“ሁላችሁም በኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ስለሆናችሁ በአይሁዳዊና በግሪካዊ፣ በአገልጋዩና በጌታ፣ በወንድና በሴት መካከል ምንም ልዩነት የለም” (ገላ. 3፡28)፡፡
የምሥራቅ አፍሪካ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤዎች ሕብረት ማለትም አመሰያ የኤርትራ፣ የኢትዮጵያ፣ ማላዊ፣ ኬኒያ፣ ታንዛኒያ፣ ሱዳንና ደቡብ ሱዳን፣ ኡጋንዳ እንደዚሁም ዛንቢያን እንዲሁም ተባባሪ አባል ሀገራት የሆኑትን ሱማሌያ እና ጂቡቲ ጳጳሳት ጉባኤዎችን በተገኙበት “በእግዚአብሔር ላይ የተመሰረተ ህያው ብዝኀነት፣ ሰብዓዊ ክብር፣ ሰላማዊ አንድነት በአመሰያ ሀገራት” በሚል ርዕስ ከሐምሌ 6-16 ቀን 2010 ዓ. ም. በአዲስ አበባ ከተማ በተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን የስብሰባ አዳራሽ 19ኛውን ጠቅላላ ጉባኤውን አድርጓል፡፡
መግቢያ
በአመሰያ ቀጠና ለሚገኙ የእግዚአብሔር ቤተሰቦችና በጎ ፈቃድ ላላቸው ወገኖች ሁሉ፡፡ እኛ የአመሰያ ቀጠና ካቶሊክ ጳጳሳት የበላይ ጠባቂዎቻችን ከሆኑት ብፁዓን ካርዲናሎች ጋር ሆነን በጌታችን በመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰላምታ እናቀርብላችኋለን፡፡ ሰላም ለእናንተ ይሁን፡፡
የቅዱስ አባታችን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮ በሲኖዶሳዊነት (አብሮ መጓዝ) ላይ ያላቸው አስተምሮና የእርሳቸው አባታዊ ቡራኬና መንፈሳዊ አመራር በፀሎት መንፈስ ሆነን እያመሰገንና እያደነቅን የቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮ በኢትዮጵያ እንደራሴ የሆኑት የቅድስት መንበር አምባሳደር ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ ሊዊጂ ቢያንኮ፣ ከቅድስት መንበር (ቫቲካን) የመጡት የስብከተ ወንጌል ጽ/ቤት ዋና ፀሐፊ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ፕሮታዜ ሩጋምብዋ እንደዚሁም በቫቲካን የሁለንተናዊ የሰው ልጅ ዕድገት ጽ/ቤት ዋና ፀሐፊ የሆኑት ሞንሲኞር ብሩኖ ማርዬ ዱፌ እና ብፁዕ ካርዲናል ዮሴፍ ቶቢን የአሜሪካ ካቶሊካውያን ጳጳሳት ጉባኤ ተወካይ የአፍሪካ የድጋፍ ፈንድ ንዑሳ ኮሚቴ ሰብሳቢ በመካከላችን መገኘት ትልቅ ጥንካሬን ሰጥቶናል፡፡
አመሰያን በመሰረቱት አባቶች መንፈስ እና ራዕይ በመመራት የቀጠናችን የጋራ የሆኑ መንፈሳዊና ማህበራዊ ጉዳዮቻችንን ወደፊት ለማስኬድ ቁርጥ አቋም ወሰደናል፡፡

1. ምስጋና
በአመሰያ ቀጠና የምንገኝ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጳጳሳት ምድረ ቀደምት ለሆነችው ለኢትዮጵያ ሕዝቦች ልዩ አድናቆት አለን፡፡ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጳጳሳት፣ ካህናት፣ ገዳማውያን/ያት፣ ምእመናን፣ የኢትዮጵያ ፌዲራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና በጎ ፍቃድ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ሁላችሁ 19ኛው የአመሰያ ጠ/ጉባኤ በኢትዮጵያ በልዩ ዝግጀት ተዘጋጅታችሁ እንዲከናወን ስላደረጋችሁ ከልብ እናመሰግናችኋለን፡፡ እንደዚሁም አጋር ድርጅቶችንም ለጉባኤው መሳካት ላደረጋችሁት ድጋፍ ከልብ እናመሰግናለን፡፡

አመሰያን ላለፉት አራት ዓመታት በሊቀ መንበርነት የመሩና የአገልግሎት ጊዜያቸውን በመጨረስ ለተረኛው ያስረከቡትን ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካዊያን፣ የሥራ ዘመናቸውን ያጠናቀቁ የሥራ አስፈፀሚ የቦርድ አባላትን፣ የአመሰያ ዋና ፀሐፊ፣ የኢትዮጵያ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤና ጠቅላይ ጽ/ቤቱን፣ የአመሰያ ጉባኤ አዘጋጅ ዓቢይ ኮሚቴና ንዑሳን ኮሚቴዎች ሁሉ እናመሰግናለን፡፡ እግዚአብሔር ሁላችሁን ይባርካችሁ፡፡
2. የእግዚአብሔር ሕዝብ ህያው ብዝኀነት
የአመሰያ ቀጠና ብዝኀነት በስፋት የሚታይበት ነው፡፡ ይህ ብዝኀነት አወንታዊ የሆነና ልንለያይበት ሳይሆን ልንደሰትበት የሚገባ ነው፡፡
እንደ ቤተክርስቲያናችን አስተምሮ ብዝኀነት የእግዚአብሔር የፍጥረት ዕቅድና ጥበብ ነው በሰዎች መካከል ያለው ልዩነት ለመደጋገፊያ እንዲሁም ካንዱ የጎደለውን አንዱ ሊያሟላበት ነው (Complimentarily)፡፡
ስለዚህ እንደ እረኞች የሰውን ልጅ ክብር የሚነኩ በብዝኀነት ላይ የሚደረጉ ወንጀሎችና አሉታዊ የሆኑ ከአካሄዶችን እናወግዛለን፡፡ ቤተክርስቲያን የምታስተምረውን ትምህርት በመንተራስ ማለትም ሰዎች ሁሉ አንደ ነፃ ፍጥረታት መጀመሪያ አላቸው፤ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ የዳኑ ናቸው መጨረሻቸውም አንድ ነው ስለዚህ ሰዎች እኩል ክብር አላቸው፡፡ በአመሰያ ቀጠና የሚገኙ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ሁሉ ይህንን ትምህርት በታላቅ እምነት ይይዙትና ይኖሩበት ዘንድ በማህበረሰቡም ውስጥ ሠርፆ ይገባ ዘንድ ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪ እናቀርባለን፡፡
በዚህ ምክንያት ማንኛውም አይነት አሉታዊ የሆኑ ከዘር ጋር የተያያዙ ማህበረሰብን የሚከፋፍሉ ሆኔታዎች እናወግዛለን፡፡

3.እኩል ክብር (Equal Dignity)
በተራ ቁጥር ሁለት በተገለፀው ስለሰው ልጆች ክብር ያለው የቤተክርስቲያን አስተምሮ በተከተለ መልኩ እኛ የአመሰያ ጳጳሳት የቫቲካ ጉባኤን አስተምሮ በምላት እንቀበላለን፡፡ ተገቢ የሆኑ ልዩነቶች በሰው ልጆች መካከል ቢንፀባረቅም የሰው ልጅ ክብር ተገቢ የሆነ ሰብዓዊነት የሞላበት ሁኔታዎች ለእያንዳንዱ እንዲመቻች የግድ ይላል፡፡ የአንድ የሰው ልጅ ቤተሰብ በሁኑ ሰዎች ወይም ቡድኖች መካከል የሚታይ የተዛባ የኤኮኖሚ ወይም ማህበራዊ ልዩነት እንቅፋትን ይፈጥራል፡፡
ማህበራዊ ፍታዊ ተጠቃሚነትን ይጎዳል፣ የሰው ልጅ ክብርን ሰላምን ይፀረራል(GS29) ስለሆነም ለሁሉም ካቶሊካውያን እና በጎ ፈቃድ ላላቸው ወገኖች ሁሉ አቤት የምንለው ሁሉም የሰው ልጅ እኩል ክብር ይጠብቁ ዘንድ፣ ከፍ ያደርጉ ዘንድ ለዚህ እውነት ራሳቸውን ያስገዙ ዘንድ ነው፡፡ ሁሉም ሰው እኩል በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ ነውና፡፡
የኤኮኖሚና የማህበራዊ ዕድገት እንዲሁም የፖለቲካ ዕድገትና የባህል ዕድገት በማህበረሰብ ውስጥ ሊታዩ የሚችሉት የሰው ልጅ ክብር ከመጠበቅ ጋር ተያይዘው ብቻ ነው፡፡
4.ሁለንተናዊ የሰው ልጅ ዕድገት
እንደ አመሰያ ጳጳሳት መርህ የሰው ልጅ ሁለንተናዊ ዕድገት ማለት የኤኮኖሚ ዕድገት ብቻ ሳይሆን እውነተኛ የሰው ልጅ ሁለንተናዊ ዕድገት በተመለከተ ቤተክርስቲያን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መሰረት በማድረግ ትነሳለች
1. በሰው ልጅ ላይ ያተኮረ
2. ሁለንተናዊነት (Holistic)
3. ሁሉን የሰው ልጅ የህይወቱ ጉዳይ አጠቃሎ የሚይዝ
4. ወደ ጋራ ጥቅም የሚመራ መሆን አለበት (general to common good)
ስለዚህ በካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን አስተምሮ እየተመራን በቀጠናችን አወንታዊ የሆነ ህያው ብዝኀነት፣ ለሰው ልጆች ሁሉ እኩል ክብር፣ በእግዚብሔር የተመሰረት ሰላማዊ አንድነት የሰው ልጅ ሁለንተናዊ ዕድገት ለማበልፀግ በርትተን እንስራለን፡፡

5. ሰላማው አንድነትን ማጠናከር
የቤተክርስቲያን የሰላም ግንባታ ሥራን አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡ ይህ የሰላም ግንባታ ተግባር ደግሞ በ4 መርሆች ላይ የተመሰረተ ነው፡፡
1) ለሰው ልጅ የተሰጠው እኩል ክብር ዕውቅና መስጠትና መንከባከብ
2) የሰው ልጅ ሁለንተናዊ ዕድገት ማጠናከር
3) በሰላም ዙሪ የሚሰሩ ዓለም አቀፍ ተቋማት መደገፍ
4) በአመሰያ ሀገራት የይቅርታ የምህረት መንፈስ እንዲነግስ መስራት

6. በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ወንድሞችና እህቶች ህብረት
በአዲስ አበባ በተከናወነው ጉባኤያችን ወቅት የሁለቱ ሀገሮች ሕዝቦች ለ20 ዓመታት የተለያዩበትን ነገር በመተው ወደመቀራረብ መምጣታቸውን መስክረናል፡፡ እነዚህ ሁለቱ ሀገሮች ወደ ሰላምና ውይይት መምጣታቸው በታላቅ ደስታ ተቀብለናል፡፡ በሁለቱም ሀገሮች የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በወንድማማቾችና እህትማማች ሕዘቦች መሀከል የተፈጠረውን ጦርነት ለማውገዝ ድምጻቸውን ከፍ አድረግው ሲናገሩ ኖረዋል፡፡ በጋራም ሆነው እየረወየየ በጸሎትም ስማጸኑና ለሕዝቦቻቸው ተስፋ እየሰጡ ቆይተዋል፡፡
በህዳር ወር 2010 ዓ. ም. ኤርትራን ሊጎበኝ የሄደው የአሜሲያ ልዑክን እናመሰግናለን “ይህ የእርቅና የሰላም ውይይት እየቀጠለ ያለ ስለሆነ የሚመለከተው ሁሉ ፍትህ እና ሰላም እንዲሰፍን ያደርጉ ዘንድ እንዲሁም በዚህ ውይይት የሁለቱም ሀገር ሕዝቦች በንቃት እንዲሳተፉ ይደረግ ዘንድ የሕዝቦች ድምፅ ይሰማ ዘንድ እንዲሁም በእሥርና በግዞት ያሉ ሁሉ ከቤተሰቦቻቸው ይቀላቀሉ ዘንድ እንጠይቃለን፡፡ በሁለቱ ሀገሮች የተደረገው እርቅ አፍሪካውያን ችግሮቻቸውን በራሳቸው አቅም የመፍታት ጥበብ እንዳላቸው ያሳየን ነው፡፡

7. ደቡብ ሱዳን
በደቡብ ሱዳን በተጀመረው የሠላም ውይይት ደስተኞች ነን “ይህ የሠላም ውይይት ፈጣን እና ዘላቂ ሠላም ያመጣ ዘንድ በጸሎት መትጋታችንን እንቀጥላለን” የሕዝቦች ሰቆቃና የንፁሀን ሞት ባፋጣኝ መቆም አለበት፡፡
በምሥራቅ አፍሪካ እንደካቶሊካውያን ጳጳሳት እኛ በደቡብ ሱዳን ሠላም ይሠፍን ዘንድ የምንችለውን እና የሚፈለግብንን ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ ነን፡፡ በምሥራቅ አፍሪካ የሚገኙ ካቶሊካውያን ሁሉ ለደቡብ ሱዳን እንዲጸልዩ እንጠይቃለን፡፡

8. ቤተሰብና ጋብቻ
ቤተሰብ የቤተክርስቲያንና የማህበረሰብ መነሻ ማዕከል መሆነን ጠንቅቀን እናውቃን፡፡ ሠላም ያለው የጸና ቤተሰብ ለቀጠናችን እንዲሁም ለዓለም ሁሉ ለህያው ብዝነት ለሰብአዊ ክብርና ለሠላማዊ አንድነት መሠረት ነው፡፡ ሆኖም ግን ቤተሰብ በዛሬው ዘመን ብዙ ተግዳሮቶችን እያስተናገደ ነው፡፡ ድህነት፣ ሥራ አጥነት፣ በማህበረሰቡ የሚስተዋሉ ልዩነቶች ሰፋ እያሉ እየመጡ ናቸው፡፡ እንደ እረኞች ቤተሰብን የሚያንጹ የሚያፀኑ ማንኛውም የድጋፍና የትምህርት ፕሮግራሞች እንዲነደፉ እንደግፋለን፡፡ ተቋማቶቻችን ሁሉ ለቤተብ ሐዋርያዊ አገልግሎት ቅድሚያ እንዲሰጡ እናደርጋለን፡፡ በቤተሰብ ሥልጠና እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ዕድገት ከሚሠሩ ተቋማት ጋርም በጋራ እንሠራለን፡፡
ይቀጥላል………

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *