የ2010 ዓ.ም የመስቀል በዓል ተከበረ

የ2010 ዓ.ም የመስቀል በዓል ተከበረ

በመስከረም ወር ከሚከበሩት ታላላቅ በዓላት የመስቀል በዓል አንዱ ነው፡፡ ካቶሊካዊትም ቤተክርስቲያን እንደሌላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በዓሉን በጋራ በታላቅ መንፈሳዊነት ታከብረዋለች፡፡ ለዚሁም መስከረም 16 ቀን 2010 ዓ.ም. የመስቀል ዋዜማ (የደመራ በዓል) በመላው ካቶሊካዊት ሀገረ ስብከቶች እንደየ አካባቢው ባሕልና ወግ መንፈሳዊነት ይዘቱን ሳይለቅ  ተከብሮ ውሏል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ  በጽዮን ማርያም ቁምስና በተደረገው በዚሁ ደመራ የማብራት ሥነ ስርዓት ከሁሉም ቁምስና የተወጣጡ ምዕመናንና በጎ ፈቃድ ያላቸው ወገኖች   ተገኝተው ነበር፡፡ የቤተክርስቲያንን ጥሪ በመቀበል በዓሉን ለማክበር በተለያየ የመጓጓዣ ትራንስፖርት በመጠቀም ቦታው ድረስ በመምጣት ምዕመናን ተገኝተዋል፡፡ በዝግጅቱ ስለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል የፀጋ ምንጭነት ሃያልነት ቤዛነት ትምህርት በክቡር አባ ተስፋዬ ወ/ማርያም የአዲስ አበባ ሀገረስብከት እንደራሴ የቀረበ ሲሆን ይህን በዓል ስናከብር በተለያየ መከራ ውስጥ የወደቁትን መስቀላቸው የከበደባቸውን  ወንድሞቻችንና እህቶቻችንን ቀርበን እንድናግዛቸው ጠይቀዋል፡፡ ከዚያም ደመራው በካህናት ከተባረከ በኋላ ችቦ በማቀጣጠል  ደመራው ከተዞረ በኋላ ደመራው እንዲቀጣጠል አድርገዋል፡፡ በዚሁ ጊዜ ወጣት መዘምራን የመስቀል ክብር በተመለከተ መስቀል ኃይላችን ነው፣ መስቀል ቤዛችን ነው፣ መስቀል መድኃኒታችን ነው በማለት ዝማሬ አቅርበዋል፡፡

በዓሉ ቀጥሎ መስከረም 17 ቀን በሁሉም ሀገረስብከቶች በታላቅ መንፈሳዊነት   ተከብሮ ውሏል፡፡ በልደተማርያም ካቴድራል  ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካውያን ዘኢትዮጵያ  ሥርዓተ ቅዳሴውን የመሩ ሲሆን በዓሉን አስመልክቶ ቃለ ምዕዳን አቅርበዋል፡፡ ብፁዕነታቸው በመልዕክታቸው መስቀል ለእኛ ለክርስቲያኖችና በጎ ፈቃድ ላላቸው ወገኖች ሁሉ ቤዛ፣ ሃይል፣ ተስፋ መሆኑን ለደኀንነታችን ወሳኝ መሆኑን በመግለጽ እንደ ማርያም በመስቀል ስር በመሆን ከክርስቶስ ጋር እስከመጨረሻው መሆን ለነፍስም ሆነ ለአካላችን ሰላምና እረፍት እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ በተመሳሳይ የክርስቶስ መስቀል መገኘት ታሪካዊነት በመግለጽ ቅድስት እሌኔ፤ ንጉስ ቆስጠንጢኖስ ለክርስትና ሃይማኖት ያደረጉትን መልካም ተግባር በመግለጽ ዛሬም እኛም በተሰጠን ችሎታ ድርሻችንን ለክርስትና መስፋፋት እንድናበረክት ጠይቀዋል፡፡ እንዲሁም መስቀልን ስናስብ የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  መሰቀል የተደረገውን ከባድ መከራ ብቻ ሳይሆን ዛሬ በገሀዱ ዓለም በግልም ሆነ በማህበረሰብ ደረጃ የሚደርስብንን፤ክርስቶስ እንዳስጠነቀቀን በሕይወት ዘመን የሚያጋጥመንን መስቀል(አስቸጋሪ ሕይወት) እንዳለ ተረድተን  እግዚአብሔር ትዕግስትንና ፅናትን እንዲሰጠን ተግተን መፀለይ እንዳለብን አሳስበዋል፡፡

በመስከረም አጥቢያ በአገራችን ብዙ ቦታ ተፈጥሮ ስንመለከት በአደይ አበባ አሸብርቆ ውበቱን የምናደንቅበት ወቅት ጅማሬ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ መንፈሳዊ አባቶቻችን ደግሞ አደይ አበባን  በእመቤታችን ድንግል ማርያም  ከሚመስሏት አንዱ መግለጫቸው ነው፡፡በአንድ አደይ አበባ ያሉ 8 ቢጫ አበቦች 2 መስቀል መስራት እንደሚችሉና  የክርስቶስ መስቀልን ከራሳችን መስቀል ጋር በማገናኘት ሕይወታችንን እንድንመራ ጠይቀዋል፡፡

በመጨረሻም ለመላው አገራችን ሰላም፣አንድነትና ብልጽግና በመመኘት እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ በማለት ከአባታዊ ቡራኬ ጋር  መልዕክት አሰተላልፈዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *